አርሲ ዩኒቨርስቲ በመጀመሪያ ዙር ያሰለጠናቸውን የህክምና ስፔሻሊስት ሀኪሞችን አስመረቀ

አርሲ፣ የካቲት 06/2013 (ዋልታ) – አርሲ ዩኒቨርስቲ የጤና ሳይንስ ኮሌጅ በመጀመሪያ ዙር በአራት የትምህርት ክፍል ትምህርታቸውን ሲከታተሉ የቆዩ 23 የህክምና ስፔሻሊስት ሀኪሞችን አስመረቀ።

ከተመራቂ ተማሪዎች መካከል 22ቱ ወንዶች እና 1 ሴት ሲሆኑ፣ በቀዶ ጥገና፣ በውስጥ ደዌ፣ የህፃናት ህክምና እና የማህፀንና ፅንስ ስፔሻሊቲ ዘርፍ ትምህርታቸውን የተከታተሉ መሆናቸው ተገልጿል።

በምረቃ መርኃ-ግብሩ ላይ የዩኒቨርሲቲው የሴኔት አባላት፣ የኦሮሚያ ክልል ጤና ቢሮ ኃላፊዎች፣ አባ ገዳዎች፣ ሀደ ሲንቄዎች እና የተመራቂ ቤተሰቦች ተገኝተዋል።

(በደረሰ አማረ)