የኮተቤ ሜትሮፖሊታን ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎቹን አስመረቀ

የካቲት 06/2013 (ዋልታ) – የኮተቤ ሜትሮፖሊታን ዩኒቨርሲቲ በመደበኛ፣ ተከታታይ እንዲሁም በማታ የትምህርት ፕሮግራሞች ያሰለጠናቸውን 2ሺህ 39 ተማሪዎች አስመረቀ።

በዛሬው እለት ካስመረቃቸው ተማሪዎች መካከል 2ሺህ 39ኙ ወንዶች ሲሆኑ 1ሺህ 29ኙ ደግሞ ሴቶች ናቸው፡፡

በምረቃ ስነስርአቱ ላይ የተገኙት የአዲስ አበባ ከተማ ም/ከንቲባ አዳነች አቤቤ ምሩቃኑ በሰለጠኑበት ዘርፍ ለሀገር የሚጠቅም ስራ እንዲያበረክቱ ጥሪ አቅርበዋል።

የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ዶ/ር ብርሀነ ጠና በበኩላቸው ተመራቂ ተማሪዎች የተመረቁት በቀለም ትምህርት በቻ ሳይሆን በአንድነትም በመሆኑ ህብረብሄራዊነትን የማስጠበቅ ኃላፊነት እንዳለባቸው ገልጸዋል፡፡

ብቁ ዜጋን በማምረት የእውቀት ፋና ወጊ የሆኑ መምህራንን በማፍራት አንጋፋ ስም ያለው ዩኒቨርሲቲው እስካሁን ከ80 ሺ በላይ ተማሪዎችን ማስመረቁ ተገልጿል።

(በሃኒ አበበ)