አሰልጣኝ ውበቱ አባተ ለ23 ተጫዋቾች ጥሪ አቀረቡ

ሰኔ 28/2014 (ዋልታ) በሀገር ውስጥ ሊግ በሚጫወቱ ተጫዋቾች የሚዋቀሩ ብሔራዊ ቡድኖች መካከል ለሚካሄደው የአፍሪካ ሀገራት ዋንጫ ውድድር ማጣርያ አሰልጣኝ ውበቱ አባተ ለ23 ተጫዋቾች ጥሪ አደረጉ።

ከደቡብ ሱዳን ጋር የቻን ማጣሪያ የሚጠብቀው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ስብስቡን ይፋ አድርጓል።

በአልጄሪያ አስተናጋጅነት ለሚከናወነው የቻን የአፍሪካ አገራት ዋንጫ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ከደቡብ ሱዳን ጋር የቅድመ ማጣሪያ ጨዋታ እንደሚጠብቀው ይታወቃል።

ሐምሌ 15 እና 24 ቀን 2014 ዓ.ም ለሚደረጉት እነዚህ ሁለት ጨዋታዎች የዋልያዎቹ አሰልጣኝ ውበቱ አባተ ለ23 ተጨዋቾች ጥሪ ማድረጋቸውን የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ይፋ አድርጓል፡፡

ግብ ጠባቂዎች ፋሲል ገብረሚካኤል፣ በረከት አማረ እና አላዛር ማርቆስ ጥሪ እንደተደረገላቸው ከእግር ኳስ ፌዴሬሽን ያገኘነው መረጃ አመላክቷል፡፡

ከተከላካዮችም ሱሌይማን ሀሚድ፣ ሄኖክ አዱኛ፣ ምኞት ደበበ፣ ያሬድ ባየህ፣ ሚሊዮን ሰለሞን፣ አስራት ቱንጆ፣ ረመዳን የሱፍ እና ጊት ጋትኩት በጥው ተካተዋል፡፡

ጥሪ የተደረገላቸው አማካዮች ጋቶች ፓኖም፣ከነዓን ማርክነህ፣ ሱራፌል ዳኛቸው፣፣በዛብህ መለዮ፣ በረከት ደስታ፣ አማኑኤል ዮሐንስ እና መስዑድ መሐመድ ናቸው፡፡

አጥቂዎች ደግሞ ቸርነት ጉግሳ፣ አማኑኤል ገብረሚካኤል፣ ዳዋ ሆቴሳ እና ብሩክ በየነ መሆናቸውን ተነግሯል፡፡

ጥሪ የተደረገላቸው ተጫዋቾችም ሐምሌ 4 ቀን 2014 ዓ.ም በፌዴሬሽኑ ጽሕፈት ቤት ተገኝተው ሪፖርት እንዲያደርጉ ጥር ቀርቧል፡፡