አሸባሪው የትሕነግ ቡድን በከተሞች ላይ ያደረሰውን ውድመት መልሶ ለመገንባት ያለመ መድረክ እየተካሄደ ነው

አሸባሪው የትሕነግ ቡድን

ጥር 18/2014 (ዋልታ) አሸባሪው የትሕነግ ቡድን በከተሞች ላይ ያደረሰውን ውድመት መልሶ ለመገንባት ያለመ መድረክ በደብረ ብርሃን ከተማ እየተካሄደ ይገኛል።

በውይይቱ የወደሙ ከተሞችን መልሶ ለመገንባት የሚያስችሉ አቅጣጫዎች ይቀመጣሉ ተብሎ ይጠበቃል።

በውይይቱ የኢፌዴሪ ከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስትር ጫልቱ ሳኒን ጨምሮ ሌሎች የፌዴራልና የክልል የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች መገኘታቸውን አሚኮ ዘግቧል።