ከግብርናው ዘርፍ የወጪ ንግድ ከ1 ነጥብ 3 ቢሊዮን ዶላር በላይ ገቢ ተገኘ

ጥር 18/2014 (ዋልታ) ባለፉት 6 ወራት ከግብርናው ዘርፍ ከወጪ ንግድ ከ1 ነጥብ 3 ቢሊዮን ዶላር በላይ ገቢ መገኘቱን የግብርና ሚኒስቴር አስታወቀ።

የግብርና ሚኒስትር ዑመር ሁሴን ባለፉት ስድስት ወራት ከግብርናው ዘርፍ ከወጪ ንግድ ከፍተኛ ገቢ መገኘቱን ገልጸዋል።

በዚህም በ6 ወራት ከግብርና ዘርፉ ከውጭ ንግድ 1 ነጥብ 323 ቢሊዮን ዶላር ገቢ ተገኝቷል፣ ይህም የዕቅዱ 109 በመቶ ነው ብለዋል።

የተገኘው ገቢ ከባለፈው ዓመት 6 ወር ጋር ሲነጻጸርም የ32 በመቶ ጭማሪ አሳይቷል ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡