አትሌት ልዑል ገብረሥላሴ በለንደን ማራቶን 2ኛ ወጣ

መስከረም 22/2015 (ዋልታ) ኢትዮጵያዊው አትሌት ልዑል ገብረሥላሴ በለንደን ማራቶን 2:05:12 በሆነ ሰዓት 2ኛ ወጥቷል።

ኬንያዊው አትሌት አሞስ ኪፕሩቶ 2:04:39 በሆነ ሰዓት 1ኛ በመውጣት ውድድሩን አሸንፏል።

ሌሎች ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ከ4ኛ እስከ 7ኛ ያለውን ደረጃ ይዘው ውድድሩን ያጠናቀቁ ሲሆን አትሌት ክንዴ አጣናው 4ኛ፣ አትሌት ቀነኒሳ በቀለ 5ኛ፣ አትሌት ብርሃኑ ለገሰ 6ኛ እና አትሌት ሲሳይ ለማ 7ኛ ወጥተዋል።

በተያያዘ ዜና በጣሊያን በተካሄደ የግማሽ ማራቶን ውድድር ኢትዮጵያዊያን ድል ቀንቷቸዋል።

በውድድሩ በወንዶች የአለም ሻምፒዮኑ ታምራት ቶላ የቦታውን ሰዓት በማሻሻል ሲያሸንፍ በሴቶች ደግሞ ብሩክታይት ደገፋው አሸናፊ መሆኗን የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌደሬሽን መረጃ ያመለክታል።