ከ17 ዓመት በታች የሴካፋ ውድድር ዛሬ በይፋ ይጀመራል

ከ17 ዓመት በታች የሴካፋ ውድድር

መስከረም 23/2015 (ዋልታ) ከ17 ዓመት በታች የምስራቅና መካከለኛው አፍሪካ የእግር ኳስ ማኅበራት ምክር ቤት (ሴካፋ) እግር ኳስ ውድድር ዛሬ በይፋ ይጀመራል፡፡

በአበበ ቢቂላ ስታዲየም በሚካሄደው የውድድሩ መክፈቻ ከቀኑ 7 ሰዓት ዩጋንዳ ከቡሩንዲ እንዲሁም ከቀኑ 10 ሰዓት ኢትዮጵያ ከሶማሊያ ይጫወታሉ።

በትላንትናው ዕለት ይፋ በሆነው የምድብ ድልድል በምድብ አንድ ኢትዮጵያ፣ ሶማሊያና ታንዛንያ፤ በምድብ ሁለት ዩጋንዳ፣ ቡሩንዲና ደቡብ ሱዳን ተደልድለዋል።

ውድድሩ ከመስከረም 21 እስከ ጥቅምት 9 ቀን 2015 ዓ.ም እንደሚካሄድ ቀን ተቆርጦለት የነበረ ቢሆንም በውድድሩ ይሳተፋሉ ተብሎ የሚጠበቁ 4 ብሔራዊ ቡድኖች በተለያየ ምክንያት ባለመሳተፋቸው ቀድሞ የወጣው የምድብ ድልድል በድጋሚ እጣ ወጥቶ ከዛሬ ጀምሮ በስድስት አገራት መካከል ውድድሩ እንደሚደረግ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን መረጃ አመልክቷል።

የሴካፋ ከ17 ዓመት በታች የእግር ኳስ ውድድር ከመስከረም 23 እስከ ጥቅምት 5 ቀን 2015 ዓ.ም በአበበ ቢቂላ ስታዲየም እንደሚካሄድም ተመላክቷል።

ለፈጣን መረጃዎች፦
ፌስቡክ https://bit.ly/3Ma7QTW