አትሌት ሲሳይ ለማ የቦስተን ማራቶንን ውድድርን አሸነፈ

አትሌት ሲሳይ ለማ

ሚያዚያ 7/2016 (አዲስ ዋለታ) በአሜሪካ አገር በተካሄደው የቦስተን ማራቶን ውድድር አትሌት ሲሳይ ለማ አሸነፈ፡፡

የ33 ዓመቱ አትሌት ውድድሩን ለማጠናቀቅ 2 ሰዓት 6 ደቂቃ ከ17 ሰከንድ ሲፈጅበት የቦታው 10ኛ ፈጣን ሰዓት ሆኖ ተመዝግቦለታል።

ሌላው ኢትዮጵያዊ አትሌት ሙሀመድ ኢሳ ውድድሩን ሁለተኛ ደረጃ በመያዝ ማጠናቀቅ ችሏል። ኬንያዊው ኢቫንስ ኪቤት ደግሞ ውድድሩን ሶስተኛ ደረጃ በመያዝ ማጠናቀቁን ሲቢኤስ ኒውስ ዘግቧል።

ውድድሩን በአንደኝነት ላሸነፈ አትሌት 150 ሺህ እንዲሁም ሁለተኛ ለወጣው ደግሞ 75 ሺህ የአሜሪካን ዶላር ሽልማት እንደሚያገኘ በመረጃው ተገልጿል።