የቲማቲም የጤና ጥቅሞች

1. የቆዳ ጥራትን ይጨምራል
ቲማቲም ከፍተኛ መጠን ያለውን የሊኮፔን(ጠንካራ ፀረ_ኦክሲዴሽን) ንጥረ ነገር ያለው ሲሆን ይህም ለቆዳ ጥራት ይረዳል።

2. ካንሰር ለመከላከል ይረዳናል
የተለያዩ ጥናቶች እንደሚያሳዩት ቲማቲም በሽንት ፊኛ ቱቦ ካንሰር፣ በትልቁ አንጀት ካንሰር እንዲሁም በጨጓራ ካንሰር የመያዝ እድላችንን ለመቀነስ የሚያስችል ሲሆን በተጨማሪም የሳንባ፣ የአፍ፣ የጉሮሮ፣ የአንጀት እና ሌሎች የካንሰር አይነቶችን ቀድሞ ይከላከላል።በቲማቲም ውስጥ ያለው ሊኮፔን ተፈጥሯዊ አንቲ ኦክሲደንት ሲሆን የካንሰር ህዋሶችን እድገት ለማዘግየት ጉልህ ሚና አለው::

3. ጠንካራ አጥንት እንዲኖረን ይረዳናል
ከፍተኛ መጠን ያለው የካልሲየም እና የቪታሚን_ኬ መገኛ ነው:: እነዚህ ንጥረ ነገሮችም አጥንትንም ሆነ የአጥንት ህዋሳትን ለማጠንከር እና አነስተኛ ጥገና ለማካሄድ በጣም አስፈላጊ ናቸው::

4. የልብ ችግርን ይከላከላል
ቲማቲም ቪታሚን_ቢ እና ፖታሲየም የበለፀገ ነው ቲማቲምን የልብ ችግርን፣ ስትሮክን እና ከልብ ጋር ተያያዥ የሆኑና ለሕይወትዎ አስጊ የሆኑ ችግሮችን ለመከላከል ያስችልዎታል፡፡ የኮሌስትሮል መጠንን እና የደም ግፊትን ለመቀነስ አይነተኛ ሚና አላቸው::

ቲማቲም

5. ለፀጉር እድገትና ጥንካሬ ይረዳል
በውስጡ የሚገኘው ቪታሚን_ኤ ጸጉር አንጸባራቂ እና ጠንካራ ለማድረግ ያግዛል።

6. ኩላሊትን ከበሽታ ይከላከላል
ቲማቲምን ፍሬውን አውጥቶ መመገብ የኩላሊት ጠጠር የመከሰት እድሉን ይቀንሳል::

7. ዕይታችንን ይጨምራል
ቪታሚን ኤ የዐይን ጤና ለማሻሻል አይነተኛ ሚና አለው:: በተጨማሪም፣ ቲማቲምን መመገብ የምሽት መታወርን (ናይት ብላይንድነስ) ለመከላከል ከምንመገባቸው ምግቦች አንዱ ነው:: ቲማቲም ክሮሚየም በተባለው እጅግ ጠቃሚ ማዕድን የተሞላ ነው::

8. የደም የስኳር መጠንን ይቆጣጠራል
በቲማቲም ውስጥ የለው ክሮሚየም /chromium/ የተባለ ንጥረ ነገር ለስኳር ህመምተኞች የደማቸው የስኳር መጠን የተመጣጠነ እንዲሆን ያስችላል፡፡

9. ክብደት ለመቀነስ ይረዳል
ከመጠን ያለፈ ክብደትን ለመቀነስና ለማስተካከል ይጠቅማል፤ ቲማቲም አነስትኛ የቅባ መጠን እና የኮሊስትሮን /የስብ/ ይዘቱ ዜሮ ሲሆን በአንፃሩ ደግሞ ለሰውነታችን በጣም ጠቃሚ የሆነ የፋይበርና የውሃ ይዘቱ ከፍተኛ ነው፡፡
ቲማቲምን በጥሬውም ይሁን አብስለን ስንመገብና ስናዘወትር የተስትካከለ የሰውነት አቋም እንዲኖረን ይርዳናል፡፡