አቶ ቢልልኝ መቆያ የአፍሪካ ቦክስ ኮንፌዴሬሽን ዋና ጸኃፊ ሆነው ተመረጡ

በተለያዩ የስፖርት ተቋማት በኃላፊነት ሲያገለግሉ የቆዩት ቢልልኝ መቆያ በደቡብ አፍሪካ ደርባን ኮንፌዴሬሽኑ ባካሄደዉ ስብሰባ የአፍሪካን የቦክስ ስፖርት በበላይነት የሚመራዉን ተቋም ጽህፈት ቤት በኃላፊነት እንዲመሩ ተመርጠዋል።

በስፖርቱ ዘርፍ ከ20 ዓመታት በላይ ልምድ ያካበቱት ቢልልኝ መቆያ ለረዥም ጊዜ የአትሌቲክስ ፌዴሬሽንን በጽህፈት ቤት ኃፊነት እንዲሁም የዳርት ፌዴሬሽንን በፕሬዚዳንትነት እየመሩ እንደሚገኙ ከባህልና ስፖርት ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ጠቁማል ።

የአፍሪካ ቦክስ ኮንፌዴሬሽን በቅርቡ አዲስ አበባ ላይ ባከናወነው ጠቅላላ ጉባኤ  እያሱ ወሰንን ፕሬዚዳንት አድርጎ መምረጡ የሚታወስ ነዉ።