አቶ ንጉሱ ጥላሁን በኢትጵያ የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ አምባሳደር ሞሃመድ ሳሊም አልረሺዲ ጋር ተወያዩ

ሚያዝያ 05/2013 (ዋልታ) – የስራ እድል ፈጠራ ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ ንጉሱ ጥላሁን በኢትጵያ የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ አምባሳደር ሞሃመድ ሳሊም አልረሺዲ ጋር ተወያይተዋል።

በውይይታቸው ኢትዮጵያና የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ በስራ እድል ፈጠራ ዙሪያ በጋራ ስለሚሰሩባቸው ጉዳዮች ዙሪያ መክረዋል።

ኢዜአ እንደዘገበው ሀገራቱ የሥራ ፈጠራ ዕድሎችን ለማሳደግ በሚችሉባቸው ጉዳዮች ዙሪያ የመከሩ ሲሆን፣ በቀጣይ ዘርፉን ለማዘመን በጋራ መስራት ስለሚችሉበት ሁኔታ በውይይቱ ዳስሰዋል፡፡