በትግራይ ስምንት አካባቢዎች የነበሩ የጁንታው ወታደሮች እና ጠባቂዎች ተደመሰሱ – ሌ/ጄ ባጫ ደበሌ

ሚያዝያ 05/2013 (ዋልታ) – በትግራይ ስምንት አካባቢዎች የነበሩ የጁንታው ወታደሮች እና ጠባቂዎች መደምሰሳቸውን የኢፌዴሪ ሀገር መከላከያ ሠራዊት የሠራዊት ግንባታ ዘርፍ ዋና አስተባባሪ ሌ/ጄ ባጫ ደበሌ አስታውቀዋል፡፡

የጁንታው ቡድን ወታደሮች እና ጠባቂዎች በትግራይ ሲያደርግ የነበረው የሽፍታ እንቅሰቃሴ በመከላከያ ሠራዊቱ በዘመናዊ ቴክኖሎጂ የታገዘ ውጊያ በማድረግ መሆኑ ተገልጿል፡፡

ህገ ወጥ ቡድኑ ወደ መቐለ እርዳታ እና ሌሎች ነገሮችን ለማጓጓዝ የሚያስችሉ ወሳኝ ቦታዎችን በመያዝ ሲዋጋ የነበረ ቢሆንም በመከላከያ ሰራዊቱ ተደምስሷል ነው የተባለው፡፡

አሁን ላይ የጁንታው ወታደሮች እና ጠባቂዎች በሰላማዊ መንገድ እጃቸውን እየሰጡ መሆኑ ተመላክቷል፡፡

(በመስከረም ቸርነት)