ጥቅምት 7/2014 (ዋልታ) በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን የተመራው ልዑክ በምዕራብ አርሲ ዞን ዶዶላ ወረዳ ሴሮፍታ የግብርና ምርጥ ዘር ማባዣን ጎበኘ።
ልዑኩ ከትናንት ጀምሮ በኦሮሚያ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች የሰብል ልማትን እየጎበኘ ይገኛል።
ኢትዮጵያን መለወጥ የሚቻለው ግብርና ሲዘምን በመሆኑ ይህ እውን እንዲሆን ሁሉም በየዘርፉ የሚጠበቅበትን ኃላፊነት ሊወጣ እንደሚገባው የጉብኝቱ ተሳታፊዎች መናገራቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡
የኦሮሚያ ምርጥ ዘር ኢንተርፕራይዝ በ5 የተለያዩ አካባቢዎች በ32 ሺሕ ሄክታር መሬት ላይ ምርጥ ዘር እያባዛ መሆኑ ታውቋል።