አቶ ደመቀ መኮንን ከደቡብ አፍሪካ ሪፐብሊክ ፕሬዝዳንት ሲሪ ራማፎዛ ጋር ተወያዩ

ሚያዝያ 28/2013 (ዋልታ) – ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ከደቡብ አፍሪካ ፕሬዘዳንት ሲሪል ራማፎዛ ጋር ተወያዩ፡፡
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ከደቡብ አፍሪካ ፕሬዘዳንት ሲሪል ራማፎዛ ጋር በሁለትዮሽ ጉዳዮች ዙሪያ ተወያይተዋል፡፡
አቶ ደመቀ መኮንን ከደቡብ አፍሪካ ፕሬዘዳንት ሲሪል ራማፎዛ ጋር የሁለቱን ሀገራት የረጅም ጊዜ ወዳጅነት ማጠናከር በሚቻልበት ጉዳይ ላይና በወቅታዊ ሁኔታ ዙሪያ ውይይት አድርገዋል፡፡
በሁለቱ አገሮች የሁለትዮሽ እና ቀጠናዊ ጉዳዮች ላይ ፍሬያማ ወይይት ማድረጋቸውም ተገልጿል።
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን በውይይታቸው ላይ በኢትዮጵያን ያለው ወቅታዊ ጉዳዮች በተመለከተ ገለፃ አድርገውላቸዋል።
በትግራይ ክልል ህግ የማስከበር እርምጃን ተከትሎ የሰብዓዊ እርዳታ ድጋፍ በስፋት ተደራሽ እየተደረገ መሆኑን አቶ ደመቀ አብራርተውላቸዋል።
ከሰብአዊ መብት ጋር በተያያዘ የሚነሱ ጥሰቶችን በመመርመር ተጠያቂ የሆኑትን ለሕግ ለማቅረብ መንግሥት ያለውን ቁርጠኝነት እና የተሰሩትን ስራዎች በዝርዝር ገልፀውላቸዋል።
የህዳሴ ግድብ አስመልክቶ በአፍሪካ ህብረት መሪነት የሶስትዮሽ ወገን ድርድር እንዲቀጥል ኢትዮጵያ ያላትን ፅኑ አቋም አሰረድተዋል።
ስድስተኛው ሀገራዊ ምርጫ በተሳካ መልኩ ለማካሄድ የሚያስችሉ የቅድመ ዝግጅት ስራዎች በትኩረት እየተከናወኑ መሆኑን አመልክተዋል።
አቶ ደመቀ ፕሬዝዳንት ራማፎዛ ለአፍሪካውያን ችግር አፍሪካዊ መፍትሔ መፈለግ መርሀ በማራመድ ላሳዩት የመሪነት ሚና አድናቆታቸውን መግለፃቸውን ከውጭ ጉዳይ ቃል አቀባይ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።