አዲሱ የቻይናው ውጭ ጉዳይ ሚነስትር አዲስ አበባ ገቡ

ጥር 2/2015 (ዋልታ) አዲሱ የቻይናው ውጭ ጉዳይ ሚነስትር ኪን ጋንግ ለይፋዊ የሥራ ጉብኝት አዲስ አበባ ገብተዋል።

ሚኒስትሩ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን አቀባበል አድርገውላቸዋል።

ኪን ጋንግ በኢትዮጵያ በሚኖራቸው ቆይታ የሁለቱን አገራት የሁለትዮሽ ግንኙነት በሚያጠናክሩ ጉዳዮች ዙሪያ ከኢትዮጵያ ከፍተኛ የመንግሥት ባለሥልጣናት ጋር ውይይት ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል።