የኢትዮጵያ እና የቻይና ግንኙነት አሁንም ጸንቶ ቀጥሏል – ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ

ጥር 2/2015 (ዋልታ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) ዛሬ ወደ ኢትዮጵያ የገቡትን የቻይናው ውጭ ጉዳይ ሚነስትር ቺን ጋንግ ጋር

ተወያይተዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ባስተላለፉት የእንኳን ደና መጡ መልዕክት የሁለቱ ሀገራት ግንኙነት አሁንም ጸንቶ ቀጥሏል ብለዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ የዛሬው ውይይታችን ይህንን እና በልማት የምንጋራውን ስልታዊ የጋራ ዓላማ፤ እንዲሁም አህጉራዊ እና ዓለም አቀፋዊ ትብብርን አጉልቶ አሳይቷል ብለዋል።