አዲሱ የኦሮሚያ ክልል መንግስት መስከረም 15 እንደሚመሰረት ተገለጸ

መስረከም 13/204 (ዋልታ) – አዲሱ የኦሮሚያ ክልል መንግስት መስከረም 15 እንደሚመሰረት የጨፌ ኦሮሚያ አፈ ጉባኤ ሎሚ በዶ አስታወቁ፡፡

የጨፌ ኦሮሚያ 5ኛው እና 6ኛውን የስራ ስብሰባ መስከረም 15/2014 እንደሚያካሂድም ነው ያስታወቁት፡፡
ጨፌው ከዚህ በፊት የቀረውንና እየተሰራ ያለውን ስራ እንዲሁም በአስፈፃሚ ስራ ላይ እንደሚወያይ ተነግሯል።
አዲሱ ጨፌ በሚያካሂደው ስብሰባም ለሶስቱ የመንግስት አካል እና የተለያዩ ሹመት ላይ በመወያየት የሚያጸድቅ መሆኑን አፈጉባኤዋ ተናግረዋል።

በመጨርሻም ለበፊቱ የጨፌ አባላት የሽኝት መርኃግብር ይካሄዳል ተብሏል።
በእመቤት ንጉሴ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት፦
የአማርኛ ፌስቡክ ገፃችንን ይወዳጁ ይከተሉ
ከአረብኛ ፌስቡክ ገፃችን ጋርም ይጓዙ
የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ
የዩቲዩብ ቻናላችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ
የትዊተር ገፃችንን ይከተሉ
አብራችሁን ስለሆናችሁ ደስተኞች ነን!