ድጋሚ ምርጫ የሚካሄድባቸው የምርጫ ክልሎች

መስከረም 13/2014 (ዋልታ) በሕግ በተደነገገው መሰረት 6ኛው ጠቅላላ ምርጫ ድጋሚ የሚካሄድባቸው የምርጫ ክልሎች የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ይፋ አደረገ፡፡

የምርጫ ክልሎቹም የሚከተሉት መሆናቸውን ቦርዱ አስታውቋል፡፡

  • ባስኬቶ ልዩ – ለክልል ምክር ቤት እና ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት
  • ቡሌ – ለክልል ምክር ቤት እና ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት
  • ጉመር 2 – ለክልል ምክር ቤት
  • መስቃና ማረቆ – ለክልል ምክር ቤት እና ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት

በተጠቀሱት የምርጫ ክልሎች ድምጽ አሰጣጡ መስከረም 20 ቀን 2014 ዓ.ም እንደሚከናወን ቦርዱ ጨምሮ ገልጿል፡፡