አድዋ እራስን ለሀገር መስጠትን ያስተማረ ታላቅ በዓል ነው – አምባሳደር ይበልጣል አዕምሮ

አምባሳደር ይበልጣል አዕምሮ

የካቲት 24/2013 (ዋልታ) – የአድዋ ድል በዓል የጥቁር ህዝቦች የክብርና የኩራት ምንጭ፣ አይበገሬነትን ያረጋገጠ ትልቅ  በዓል መሆኑን በሱዳን የኢትዮጵያ አምባሳደር ይበልጣል አዕምሮ ገለጹ።

125ኛው የአድዋ ድል በዓል በሱዳን የኢፌዴሪ ኢምባሲ ተከብሯል።

በሥነ-ሥርዓት ላይ ንግግር ያደረጉት በሱዳን የኢትዮጵያ አምባሳደር ይበልጣል አዕምሮ   አድዋ ሕብረ ብሔራዊ አንድነታችንን እና እራስን ለሀገር መስጠትን ያስተማረ ታላቅ በዓል ነው ብለዋል።

ከኢምባሲው የተገኘው መረጃ እንደሚያመላክተው፣ አንድነት እንደሚያድነንና ጎጠኝነት እንደሚያጠፋን በመረዳት በአንድነት ለሀገራችን ሰላምና ልማት መነሳት እንደሚገባ አምባሳደር ይበልጣል አስገንዝበዋል።