አገርን ለመጠበቅና ለመገንባት አርበኝነት ከሁላችንም ይጠበቃል – ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ

አገርን ለመጠበቅና ለመገንባት አርበኝነት ከሁላችንም ይጠበቃል፤ ያለፈውን ጀግንነት የምናቆየው ለዚህ ከተነሳን ነው ሲሉ የኢፌዲሪ ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ገለጹ።

ፕሬዝዳንቷ 80ኛ ዓመት የአርበኞች ቀንን ምክንያት በማድረግ የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።

እንኳን ለአርበኞች ቀን በደህና አደረሰን ያሉት ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ “የጥንት ኢትዮጵያ አርበኞች አገራችን ነጻነቷን ጠብቃ እንድትኖር አድርገዋል“ ብለዋል።

የጥንት ኢትዮጵያ አርበኞች አገራችን ነጻነቷን ጠብቃ እንድትኖር አድርገዋል ሲሉ ነው ፕሬዝዳንቷ የገለጹት፡፡