ኢትዮጵያና ቱርክ በትራንስፖርት ዘርፍ በጋራ ለመስራት ተፈራረሙ

ሰኔ 03/2013 (ዋልታ) – ኢትዮጵያና ቱርክ በትራንስፖርቱ ዘርፍ ቴክኒካዊ ጉዳዮች ላይ በጋራ ለመስራት የሚያስችላቸውን ስምምነት ተፈራርመዋል፡፡

ስምምነቱን ያካሄዱት የአትዮጵያ የትራንስፖርት ሚኒስትር ዳግማዊት ሞገስና የቱርክ አቻቸው አዲል ካራይስ ማይልጉሉ ናቸው።

በስምምነቱ መሰረት ቱርክና ኢትዮጵያ በትራንስፖርቱ ዘርፍ ቴክኒካዊ የትብብር ስራዎችን በጋራ እንደሚያከናውኑ የኢዜአ ዘገባ አመላክቷል፡፡