ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በዓለም አቀፍ ደረጃ በተካሄዱ ውድድሮች ድል አስመዘገቡ

ነሐሴ 23/2014 (ዋልታ) ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ትላንት ምሽት በዓለም አቀፍ ደረጃ በተካሄዱ ሶስት የተለያዩ ርቀቶች ድል አስመዝግበዋል፡፡

አትሌቶቹ ድል የተቀዳጁት በግማሽ ማራቶን፣ በማራቶንና በ1500 ሜትር ርቀት ነው፡፡

በዚህም መሰረት በአንትሪም ግማሽ ማራቶን ወንዶች፡-

1ኛ – ጀማል ይመር፣ 59:03

4ኛ – ተስፋሁን አካልነው፣ 1:01.43

በሴቶች፡-

1ኛ – ያለምዘርፍ የኋላው፣ 1:04.21

2ኛ – ፀሐይ ገመቹ፣ 1:05.00

ጀርመን ሊቨርኩሰን በተካሄደ የ1500 ሜትር ውድድር፡-

1ኛ – ነፃነት ደስታ፣ 4:07.53

አውስትራልያ በተደረገ ግማሽ ማራቶን ሴቶች፣

1ኛ – በቀለች ጉደታ፣ 1:08.05

በወንዶች፣

2ኛ – ኪሮስ አሸናፊ፣ 1:05.51

በሜክሲኮ ማራቶን ደግሞ፡-

በሴቶች፣

1ኛ – አማኔ በሪሶ፣ 2:25.05 (CR)

3ኛ – ሙሉዬ ደቀቦ፣ 2:31.07 በመሆን ማሸነፋቸውን የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌደሬሽን መረጃ ያመለክታል፡፡