ኢትዮጵያ በመጭው መስከረም የአፍሪካ ከተሞች ፎረምን ታካሂዳለች – ምክትል ጠ/ሚ ተመስገን ጥሩነህ

ምክትል ጠ/ሚ ተመስገን ጥሩነህ

ሚያዚያ 15/2016 (አዲስ ዋልታ) ኢትዮጵያ በመጭው መስከረም የአፍሪካ ከተሞች ፎረምን እንደምታካሂድ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ አስታወቁ።

በመጭው መስከረም “ዘላቂ የክትመት ምጣኔ ለአፍሪካ ትራንስፎርሜሽን – አጀንዳ 2063” በሚል መሪ ቃል የአፍሪካ ከተሞች ፎረም በአዲስ አበባ እንደሚካሄድ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው አስፍረዋል።

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ዛሬ የአፍሪካ ከተሞች ፎረም ብሄራዊ አስተባባሪ አብይ ኮሚቴ የመክፈቻና የግንዛቤ መስጫ መድረክ አካሂደናል ብለዋል።

ኢትዮጵያ እንደ ሀገር ታሪካዊት፣ የተባበሩት መንግስታት እና የአፍሪካ አንድነት ድርጅት የአሁኑ አፍሪካ ህብረት መስራች ሀገር ይህንን ከአንድ ሺህ አምስት መቶ በላይ ተሳታፊዎች እንደሚታደሙበት የሚጠበቀውን የአፍሪካ ወንድማማቾች መመካከሪያ መድረክ ለማዘጋጀት የተሰጣትን አፍሪካዊ ኃላፊነት በሚገባ ለመወጣት ዝግጁ መሆኗን በመድረኩ ተግባብተናል ሲለም ገልጸዋል።