ኢትዮጵያ በእርምጃ ውድድር የወርቅና ብር ሜዳሊያ አሸነፈች

አትሌት ምስጋና ዋቁማ

መጋቢት 11/2016 (አዲስ ዋልታ) ኢትዮጵያ በጋና አክራ እየተካሄደ በሚገኘው 13ኛው የመላ አፍሪካ ጨዋታዎች በወንዶች የ20 ኪሎ ሜትር እርምጃ ውድድር በአትሌት ምስጋና ዋቁማ የወርቅ ሜዳልያ አሸነፈች።

አትሌት ስንታየሁ ማስሬ

በሴቶች 20 ኪሎ ሜትር እርምጃ ደግሞ ስንታየሁ ማስሬ ብር ሜዳልያ ማሸነፍ መቻሏን ከኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌደሬሽን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

እስካሁን በአጠቃላይ በውድድሩ ኢትዮጵያ አምስት ወርቅ፣ ሶስት የብር እና አንድ የነሀስ ሜዳልያዎችን ማሸነፍ ችላለች።