ኢትዮጵያ ተፋሰሱን ፍትሐዊ እና ምክንያታዊ በሆነ መልኩ በጋራ የመጠቀም አቋሟ የማይናወጥ ነው – ዶክተር ስለሺ በቀለ

መጋቢት 23/2013 (ዋልታ) – ኢትዮጵያ ተፋሰሱን ፍትሐዊ እና ምክንያታዊ በሆነ መልኩ በጋራ ለመጠቀም አቋሟ የማይናወጥ ነው ሲሉ የውሃ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስትር ዶክተር ስለሺ በቀለ ገልጸዋል፡፡

የህዳሴ ግድቡን 10ኛ ዓመት አስመልክቶ  የእንኳን አደረሳችሁ መልእክት ያስተላለፉት ሚኒስትሩ ግድቡ 79 በመቶ መድረሱን አስታውቀዋል፡፡

“በሀገር ውስጥም በውጭም ሆናችሁ ይህንን በጣም አስፈላጊ የሆነ ግንባታ እየደገፋችሁ ያላችሁ ሁሉ ሰላምታችንና ምስጋናችን ይድረሳችሁ” ሲሉ በትውተር ገጻቸው አስፍረዋል፡፡

ለታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የምናደርገው ታላቅ ንቅናቄና ድጋፍ እንዲሁም ለሰላም የምናደርገው ቀናዒነት የበለጠ ተጠናክሮ መቀጠል አለበትም ነው ያሉት፡፡