ኢንጂነር ታከለ ኡማ በጋምቤላ ባህላዊ የወርቅ ማምረቻና መሸጫ ቦታን ጎበኙ

የማዕድንና ነዳጅ ሚኒስትር ኢንጂነር ታከለ ኡማ ከጋምቤላ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ኡመድ ኡጁሉ ጋር በመሆን በጋምቤላ በጋምቤላ ባህላዊ የወርቅ ማምረቻና መሸጫ ቦታን ጎብኝተዋል።

ሚኒሰትሩ በማህበራዊ የትስስር ገጻቸው “ከሞቃታማው አየሯ ጀርባ ድንቅ ህዝብና ድንቅ ተፈጥሮ በያዘችው ጋምቤላ ክልል ተገኝቻለሁ” በማለት አስፍረዋል፡፡

ጋምቤላ በወርቅና በተፈጥሮ ጋዝ ማዕድናት የታደለች ብትሆንም ከሀብቱ ጋምቤላም ኢትዮጵያም በሚገባው ልክ እየተጠቀሙ አይደለም ያሉት ሚኒስትሩ “በጉብኝቴ ሕገወጥ አዘዋዋሪዎችና የመሰረተልማት ችግር እንቅፋት መሆናቸውን ተረድቻለሁ፤ አብዛኛው የወርቅ ምርት በሕገወጥ መንገድ ከሀገር እየወጣ ይገኛል፤ ይህን አካሄድ ስርአት እናስይዛለን” ብለዋል።

ኢንጂነር ታከለ ባህላዊ አምራቾችንም በተገቢው መንገድ በመደገፍ አቅማቸው እንዲያድግ እንሰራለን እና በየትኛውም የሀገራችን ጫፍ የሚገኝ የተፈጥሮ ፀጋ በተገቢው መንገድ ለህዝብና ሀገር ጥቅም እንዲውል ማድረግ የቅድሚያ ስራቸው እደሆነ ገልጸዋል።