የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት በ’ገበታ ለሀገር’ ለመሳተፍ ገንዘብ ገቢ ላደረጉ ተቋማት አድናቆቱን ገለፀ

የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት በ’ገበታ ለሀገር’ ለመሳተፍ ገንዘብ ገቢ ላደረጉና ደረሠኙን በመላክ ላሳወቁ ተቋማት አድናቆቱን ገልጿል፡፡

ተቋማቱ የሚከተሉት ናቸው፡-

  • የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እና የባንኩ ማሕበረሰብ – 1.1 ቢሊየን ብር
  • የኢትዮጵያ ልማት ባንክ – 90 ሚሊየን ብር
  • የከፍተኛ ት/ት እና ሳይንስ ሚኒስቴር ማኅበረሰብ – 5 ሚሊየን ብር
  • የኢትዮጵያ መድን ድርጅት – 15 ሚሊየን ብር
  • ሞሐን ፒ.ኤል.ሲ – 10 ሚሊየን ብር
  • አቮን ኢንደስትሪስ ፒ.ኤል.ሲ – 5 ሚሊየን ብር
  • ላየንስ ኢንተርናሽናል ትሬዲንግ ፒ.ኤል.ሲ – 5 ሚሊየን ብር
  • አማራ ብድር እና ቁጠባ ተቋም – 20 ሚሊየን ብር
  • ኤ.ቢ.ኤች ፓርትነርስ – 10 ሚሊየን ብር
  • የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መስተዳድር ምክር ቤት – 5 ሚሊየን ብር
  • ስታር ቢዝነስ ግሩፕ – 10 ሚሊየን ብር
  • የኢንደስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን – 10 ሚሊየን ብር
  • የኢንደስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ሠራተኞች – 5.2 ሚሊየን ብር

ሌሎች ተቋማትም የ5 እና የ10 ሚሊየን ብር አስተዋጾአቸውን ባንክ ያስገቡበትን ደረሰኝ በdineforethiopia@pmo.gov.et እንዲያደርሱት ጽ/ቤቱ ጠይቋል።