ባለን ሀብት እና የሰው ኋይል ከድህነት መላቀቅ ይቻላል – ጠ/ሚ ዐቢይ

ጥቅምት 4/2014 (ዋልታ) ባለን ሀብት እና የሰው ሀይል ከድህነት መላቀቅ ይቻላል ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) ገለጹ፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በሞጀ ከተማ እየተመረተ የሚገኘውን የአቮካዶ ምርት ጎብኝተዋል ፤ በዚህም ከድህነት ለመላቀቅ የሚገጥሙ ችግሮች በማለፍ እንደሆነ አስገንዝበዋል።
ይህ የአቮካዶ ምርቱ ከእስራኤል ሀገር የመጣ እና በዓለም ገበያ ላይ ተፈላጊ የሆነ ሲሆን፣ በአጠቃላይ በ6 ሺሕ ሄክታር መሬት ላይ የአከባቢው አርሶ አደሮች እያለሙ ይገኛሉ።
በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) የተመራው የክልል ርዕሳነ መስተዳድሮች እና የከተማ አስተዳደሮች የተሳተፉበት ጉብኝት ተጠናቋል።
በሚልኪያስ አዱኛ