ኦቢኤን ግንባር ድረስ በመጓዝ ለዘገቡ ጋዜጠኞች የምስጋና ዝግጅት አካሄደ

የኦሮሚያ ብሮድካስቲንግ ኔትዎርክ (OBN) በሰሜን ኢትዮጵያ በህወሃት ጁንታ ቡድን ላይ መንግስ በወሰደው ሃገርን የማዳን የህግ ማስከበር ተግባር ላይ መረጃዎችን ለህዝብ ለማድረስ ከመከላከያ ሰራዊት ጎን በመጓዝ ዘገባ ሲሰሩ ለነበሩ ጋዜጠኞች የምስጋና ዝግጅት አካሂዷል፡፡

በዝግጅቱ ላይ የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳደር ሽመልስ አብዲሳን ጨምሮ ከፍተኛ የመከላከያ ሰራዊት ጄነራሎች፥ ከፍተኛ የመንግስት የሥራ ኃላፊዎች፣ የሚዲያ ኃላፊዎች፣ አባ ገዳዎች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።

ኦቢኤን በ13 የሃገር ውስጥና የውጭ ሃገር ቋንቋዎች እየሰራ መሆኑም ተገልጿል።

(በምንይሉ ደስይበለው)