ከለውጡ በኋላ የተገኘውን ድልና ስኬት ለማስቀጠል ያለመ የድጋፍ ሰልፍ በኦሮሚያ ክልል ተካሄደ

መጋቢት 24/2015 (ዋልታ) ከለውጡ በኋላ የተገኘውን ድልና ስኬት ለማስቀጠል ያለመ የድጋፍ ሰልፍ በኦሮሚያ ክልል ተካሂዷል፡፡

በዚህም መሰረት በቢሾፍቱ፤ አምቦ፤ ቄለም ወለጋ፤ አዳማ፤ ቡኖ በደሌ እና ጉጂ ዞን፤ ባሌና ምዕራብ ጉጂ ዞኖች፤ ሮቤ ከተማ፤ ሆለታ ከተማ ተካሂዷል፡፡

በተጨማሪም ነቀምቴ፤ ሞጆ ፤ የምስራቅ ቦረና እና ኢሉ አባቦር ዞኖች እንዲሁም በተለያዩ የኦሮሚያ ዞኖችና ከተማ አስተዳደሮቸ ተካሂዷል፡፡

በድጋፉ ሰልፍ ላይ በሚሊየን የሚቆጠሩ ዜጎች በነቂስ ወጥተው ለለውጡ ያላቸውን ድጋፍ የተገለፁ ሲሆን የተገኙ ድልና ስኬቶችን የሚያንጸባርቁ መልዕክቶች ተላልፈዋል፡፡

እንዲሁም ነዋሪዎቹ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በሳል አመራር እንደ ሀገር ለውጥ የተመዘገበበት ወቅት መሆኑን ያመላከቱ ሲሆን በመሰዋዕትነት የተገኘውን ድል ሁላችንም በመተባባር ልንጠብቀው እንደሚገባ በመልዕክታቸው ጥሪ አስተላልፈዋል፡፡