ከመቼውም ጊዜ በተሻለ አብሮነታችን በማጉላት አሻራችንን በጋራ ማኖር አለብን – ም/ከንቲባ አዳነች አበቤ

ግንቦት 26/2013 (ዋልታ) – የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ አዳነች አበቤ ኢትዮጵያዊን የህብረ ብሄራዊ ወንድማማችነት የምናሳይበት አንድነታችንን የሚያጠናክር ከመቼውም ጊዜ በተሻለ ለሀገር ልማት በጋራ የምንተጋበት አብሮነታችን የሚጎላበት እንዲሆን ሁላችንም አሻራችንን በጋራ ማኖር አለብን ብለዋል።
የሀላባ ህዝብ የልማት ማህበር የምክክር መድረክ በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው፡፡
የልማት ማህበሩ በአዲስ አበባ ለሚገነባዉ የባህል ማዕከል የመሬት ይዞታ ማረጋገጫ ካርታ ምክትል ከንቲባ አዳነች አበቤ ለልማት ማህበሩ አስረክበዋል።
የባህልና ቱሪዝም ሚኒስትር ዶ/ር ሂሩት ካሳው የሚገነባው የባህል ማዕከል የዞኑን የክልሉን እና የኢትዮጵያን ባህል የሚያስተዋውቅ አዲስ አበባን የባህል ማዕከል ለማድረግ እየተሰራ ያለውን ስራ የሚያግዝ የቱሪዝም መስህብ የሚጨምር ይሆናል ብለዋል።
የሀላባ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ዶ/ር መሀመድ ኑርዬ የሚገነባው የባህል ማዕከል የዞኑን የክልሉን እና የኢትዮጵያን ባህል የሚያስተዋውቅ አዲስ አበባን የባህል ማዕከል ለማድረግ እየተሰራ ያለው ስራ የሚያግዝ ይሆናል ብለዋል።
የልማት ማህበሩ በጤና፣ በትምህርት፣ በመንገድ፣ በውሃና ሌሎች በዞኑ ያሉ የመሰረተ ልማት ችግሮችን ለመፍታት እና ተደራሽ ለማድረግ እየተሰራ እንደሆነም ገልፀዋል።
የሀላባ ህዝብ ልማት ማህበር ሥራ አስኪያጅ አምሩላ ጠለሀ በበኩላቸው የልማት ማህበሩ በዞኑ የተጀመሩ የልማት ስራዎችን የበለጠ አጠናክሮ እንደሚሰራና የሃላባን ቋንቋ፣ ባህል ወግና እሴት ተጠብቆ ለትውልድ እንዲተላለፍ ይስራል ብለዋል።
በመርሃ ግብሩ የአዲስ አበባ ከተማ አሰተዳደር ምክትል ከንቲባ አዳነች አበቤ፣ የባህልና ቱሪዝም ሚኒስትር ዶ/ር ሂሩት ካሳው፣ የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ሚኒስትር ኢንጂነር አይሻ መሀመድ፣ የፌደራልና የክልሉ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች፣ የሃይማኖት አባቶች፣ የሃገር ሽማግሌዎችና የዞኑ ተወላጆችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።
(በህይወት አክሊሉ)