ከመጋቢት እስከ መጋቢት የተሰኙ የ3 መፅሐፍት ምረቃ

ከመጋቢት እስከ መጋቢት መፅሐፍት ምረቃ

መስከረም 18/2014 (ዋልታ) በጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ፕሬስ ሴክሬታሪያት የተፃፉ ከመጋቢት እስከ መጋቢት የተሰኙ ሦሰት መፅሐፍት ተመረቁ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) ከመጋቢት 24/2010 ዓ.ም እስከ መጋቢት 2013 ዓ.ም ያደረጓቸውን ንግግሮች ያካተቱ ሶስት ቅፅ መፅሐፍት ናቸው በዛሬው ዕለት የተመረቁት፡፡

መፅሐፍቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ከበዓለ ሲመታቸው ጀምሮ ያደረጓቸው ከ176 በላይ ንግግሮች፣ መግለጫዎችና አጫጭር መልዕክቶች ተካተውባቸዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በአማርኛ፣ ኦሮምኛ፣ ትግርኛና እንግሊዘኛ ቋንቋዎች ያደረጓቸው ንግግሮችም በመፅሐፍቱ ተካተዋል፡፡

ከመፅሐፍቱ ሽያጭ የሚሰበሰበው ገቢ በጦርነቱ ከቀያቸው ለተፈናቀሉና ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖች እንደሚውል ተገልጿል፡፡

በሳሙኤል ሓጎስ