ከሚሴ ከተማ ወደ ቀድሞ ሰላሟ እየተመለሰች መሆኑን የከተማዋ ነዋሪዎች ተናገሩ

መጋቢት 16/2013 (ዋልታ) – በከሚሴ ከተማ ከሰሞኑ የነበረው አለመረጋጋት እየረገበ መሆኑንና ከተወሰኑ ተቋማት ውጭ በአብዛኛው ወደ ሙሉ የእለት ከእለት እንቅስቃሴ መመለሱን ነዋሪዎች ተናግረዋል፡፡
የከሚሴ ከተማ ነዋሪ አሕመድ ሙሀመድ ሰላሙን ቀጣይነት ያለው ለማድረግ ሁሉም መረባረብ እንዳለበት ጠቁመዋል፡፡
ሌላኛው አብመድ ያነጋገራቸው መላከ ገነት ደጀን ተስፋዬ አጥፊዎችን ለሕግ ለማቅረብ በአግባቡ ሊሠራ ይገባል ብለዋል፡፡
የከሚሴ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባና የሕዝብ ሰላምና ደኅንነት ግንባታ ጽሕፈት ቤት ኀላፊ አቶ ጀማል ኢብራሂም በከሚሴ ከተማ የሚታየውን አንፃራዊ ሰላም ቀጣይነት እንዲኖረው ለማድረግ ከሌሎች የጸጥታ አካላት ጋር በጋራ እየተሠራ መሆኑን መናገራቸውን አብመድ ዘግቧል፡፡