5ኛው የህዝብ ተወካዮች ም/ቤት 6ኛ አመት የስራ ዘመን 12 ኛ መደበኛ ሰብሰባውን አካሄደ

መጋቢት 16/2013 (ዋልታ) – 5ኛው የህዝብ ተወካዮች ም/ቤት 6ኛ አመት የስራ ዘመን 12 ኛ መደበኛ ሰብሰባውን አካሄደ።
ም/ቤቱ መስከረም 28 ቀን 2013 ዓ.ም ባካሄደው 1ኛ መደበኛ ስብሰባ በንግድ ህግ ማሻሻያ ረቂቅ አዋጅ ላይ ውይይት ካካሄደ በኋላ ረቂቅ አዋጅን ለዝርዝር ዕይታ ለንግድ እና ኢንድስትሪ ጉዳዮች ቋሚ በተባባሪነት ደግሞ ለህግ፣ ፍትህ እና ዴሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ መርቶ እንደ ነበር ይታወሳል።
በመሆኑም የንግድ ህጉ ላለፉት 62 አመታት ሲያገለግል የቆየ ሲሆን፣ ህጉን ማሻሻል አስፈላጊ በመሆኑ ምክር ቤቱ ረቂቅ ህጉን ከነማሻሻያዎቹ ተቀብሎ በሙሉ ድምፅ አፅድቆታል ::
በኢትዮጵያ እና በኡጋንዳ ሪፐብሊክ መንግስት መከከል በወንጀል ጉዳዮች የሚፈለጉ ሰዎችን አሰልፎ የመስጠት እና የወንጀል ጉዳዮች የጋራ የፍትህ ትብብር ስምምነትን ምክር ቤቱ በሙሉ ድምፅ አፅድቆታል ።
የፌደራል ጥብቅና አገልግሎት ፍቃድ አሰጣጥ እና አስተዳደር አዋጅን ምክር ቤቱ መርምሮ ለዝርዝር እይታ ለህግ ፍትህ እና ዲሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ መርቷል::
(በሜሮን መስፍን)