ከረዩ የዳቦ ማምረቻና ማከፋፈያ ተመረቀ

ታኅሣሥ 5/2015 (ዋልታ) ከ140 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ የተደረገበት ከረዩ የዳቦ ማምረቻና ማከፋፈያ ተመረቀ፡፡

በሂማ ማኒፋክቸሪግ ኩባንያ ሙሉ ወጪ እና በከተማ አሰተዳደሩ የቦታ አቅርቦት የተገነባው ማምረቻው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ በተገኙበት ነው የተመረቀው፡፡

ማምረቻው አሁን ላይ በቀን ከ150 ሺሕ እስከ 200 ሺሕ ዳቦ በማምረት ላይ ሲሆን በሙሉ አቅሙ ወደ ስራ ሲገባ በቀን 1 ሚሊዮን ዳቦ እንደሚያመርት ተጠቁሟል፡፡

ለከረዩ ዳቦ ማምረቻ እና ማከፋፈያ መንግስት የዱቄት አቅርቦት ስራ የሚሰራ መሆኑ የተነገረ ሲሆን የንግድ ቢሮ በሚያወጣው ቅናሽ የዳቦ መሸጫ ተመን እንደሚያከፋፍልም ተገልጿል፡፡

በአመለወርቅ መኳንንት