ከሳዑዲ አረቢያ ወደ አገራቸው ለሚመለሱ ኢትዮጵያዊያን ጊዜያዊ ማረፊያ ቦታ ተዘጋጀ

መጋቢት 20/2014 (ዋልታ) ከሳዑዲ አረቢያ ወደ አገራቸው ለሚመለሱ ኢትዮጵያዊያን ጊዜያዊ የማረፊያ ቦታ መዘጋጀቱን የሴቶችና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡
ከሳዑዲ አረቢያ ወደ አገራቸው የሚመለሱ ኢትዮጵያዊያን በጊዜያዊነት የሚያርፉበት ቦታ በተለምዶ ወሰን ሁለት ተብሎ በሚጠራው አካባቢ በሚገኘው ከስደት ተመላሾች ጊዜያዊ ማቆያ ቅጥር ግቢ ውስጥ ነው የተዘጋጀው፡፡
የሚኒስቴሩ ከፍተኛ አመራሮች ከስደት ተመላሾች ጊዜያዊ ማቆያ ቅጥር ግቢ በመገኘት ተመላሾችን ለመቀበል የተሰሩ የቅድመ ዝግጅት ሥራዎችን ጎብኝተዋል፡፡
ወደ አገራቸው የሚመለሱ ዜጎችን መልሶ የማቋቋም ተግባራት እንደሚሠሩም ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
ከነገ ረቡዕ መጋቢት 30 ቀን 2022 ዓ.ም ጀምሮ በመጪዎቹ 7 እስከ 11 ወራት ውስጥ ወደ 100 ሺሕ የሚጠጉ ኢትዮጵያዊያን ወደ አገራቸው እንደሚመለሱና መልሶ የማቋቋም ሥራዎች በአገር ዐቀፍ ደረጃ ይሰራሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡