ከቀያቸው ተፈናቅለው በደሴ ከተማ ለሚገኙ ወገኖች ድጋፍ ተደረገ

ነሃሴ 9/2013(ዋልታ) – ከሰሜን ወሎ ዞን ተፈናቅለው በደሴ ከተማ ለሚገኙ ወገኖች የተለያዩ አልባሳት፣ ቁሳቁሶችና ምግቦች ድጋፍ ተደረገ፡፡
በደሴ ከተማ የሚገኙ የግል ጤና ተቋማት ባለቤቶች ናቸው ከ621 ሺህ ብር በላይ በሆነ ወጪ ለተፈናቀሉ ወገኖች ለምግብ አገልግሎት የሚውልና ሌሎች አስፈላጊ ቁሳቁሶችን ድጋፍ ያደረጉት፡፡
ድጋፉን በከተማው በቅዳሜ ገበያ ትምህርት ቤት ተገኝተው አስረክበዋል።
በተጨማሪም ጤና ተቋማት ባለቤቶቹ በሙያቸውም ጭምር ለማገልገል ያላቸውን ፍላጎትና ቁርጠኝነት መግለፃቸውን ከደሴ ከተማ ኮሙዩኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡