የአፋር ግንባር ድል በምዕራብ ግንባርም ተጠናክሮ ቀጥሏል

ነሐሴ 10/2013 (ዋልታ) – በአማራ ክልል በምዕራበ ግንባር በሽብርተኛው ህወሃት ታጣቂ ቡድን ላይ በተወሰደ እርምጃ ቡድኑ ከፍተኛ የሆነ ሰብአዊና ቁሳዊ ኪሳራ ደርሶበታል፡፡
በአማራ ክልል በምዕራበ ግንባር በዛሬማ፣በጨው በር እና በር ማሪያም በተባሉ አካባቢዎች ላይ የሀገር መከላከያ ሰራዊት ፤የአየር ሀይል፣ለሰራዊቱ ደጀን የሆነው የአማራ ህዝብ፣ የክልሉ ልዩ ሀይልና ታጣቂው በመቀናጀት በሽብርተኛው ህወሃት ታጣቂ ቡድን ላይ በወሰዱት እርምጃ ሽብርተኛው ቡድን ከፍተኛ የሆነ ሰብአዊና ቁሳዊ ኪሳራ ደርሶበታል፡፡
ይህን ተከትሎም በበርካታ ተሸካርካሪዎች አስክሬኖችን ጭኖ ወደ ማይፀብሪ የወሰደ ሲሆን፤ በዚህ ውጊያ ላይ ስሙ ለግዜው ያልታወቀ አንድ የበድኑ ከፍተኛ ወታደራዊ አመራር አስክሬንም በፓትሮል ታጅቦ ወደ ማይፀብሪ ተወስዷል፡፡
በተመሳሳይ በአድርቃይ በነበሩ የታጠቂው ቡድን ላይ ጀግናው የሀገር መከላከያ ሰራዊት እንዲሁም የክልሉ ልዩ ሀይልና ሚሊሻ ሀይል የወሰደባቸውን እርምጃ የሽብርተኛው ታጣቂ ቡድን መቋቋም ባለመቻሉ አመራሮቹ የቀረ ሀይላቸው ወደ ማይፀብሪ እንዲሸሽ ተዛዝ የሰጡ ሲሆን፤ በእነዚሁ አካባቢዎች ተቆርጦ የቀረውን የአሸባሪውን ታጣቂ ሀይል እዚያወ ለማስቀረትና ለመደምሰስ እርምጃው ተጠናከሮ ቀጥሏል፡፡
በተያያዘም በጋሸና ግንባር ሳሊና እና ጎብጎብ በተባሉ አካባቢዎች በአሸባሪው ቡድን ላይ በተወሰደ የአየር ጥቃት ቡድኑ ከፍተኛ ሰበአዊና ቁሳዊ ኪሳራ የገጠመው ሲሆን፤ ይህን ተከትሎም ቡድኑ ወደ ኋላ በመሸሽ ከሰሜን ወሎ ዞን እስታይሽ፣አሁንተገኝ፣ጋሸና፣ገርገራ እና ፍላቂት ከተሞች ላይ ከመንግስት ተቋማት፣መንግስታዊ ካልሆኑ ደርጅቶችና ተቋማት እንዲሁም ከህብረተሰቡ በርካታ ንብረቶችን በመዝረፍ ቁጥራቸው በዛያለ ተሸከርካሪዎች ላይ ጭኖ ወደ ትግራይ ለመውሰድ ሲንቀሳቀስ ቲሃ የተባለ አካባቢ ቆፍጣናው የአማራ አርሶ አደሩ ንብረቱን ይዞ እንዳይሄድ በከፈተበት የደፈጣ ተኮስ ተደናግጦ ሲደናበር፤ የአማራ ልዩ ሀይልና ታጣቂው በቦታው በመድረስ ከአርሶ አደሩ ጋር በመቀናጀት በወሰዱት እርምጃ በትናንትናው ዕለት የዘረፈውን ንብረት ጥሎ አስ ወደ ተባለ ከተማ አቅራቢያ የሸሸ ሲሆን፤ ጀግናው የአማራ ክልል ልዩ ሀይልና ታጣቂው ከመከላከያ ሰራዊት ጋር በመሆን አሸባሪው ህወሃት ያሰማራውን ታጣቂ ሀይል እግር በእግር በመከታተል እርምጃ በመወሰዱ ጥቃቱ ዛሬ ቀጥሏል። ይህንን ሀይል ባለበት ለማስቀረት እየተደረገ ያለው ከፍተኛ ትንቅንቅና ተጋድሎ መቀጠሉን ምንጮቻችን ከስፍራው አረጋግጠዋል፡፡
ይህ በእንዲህ እንዳለ በአፋር ግንባርም በሀሮ መስመር በድሬእሮቃ አረርቲ በተባለች ቦታ ላይ የሽብርተኛው ህወሃት ታጣቂዎች በ8/2013 ዓ.ም ማታ ላይ የፈፀሙትን ድንገተኛ ትንኮሳ ጀግናው የሀገር መከላከያ ሰራዊት፣ ከአፋር ክልል ልዩ ሀይልና ታጣቂ ጋር በቅንጀት በወሰዱበት የአፀፋ እርምጃ ቡድኑ ሲደመሰስ፤ በርካታ የቡድኑ ታጣቂዎች ሙትና ቁስለኛ ሲሆኑ፤ ዲሽቃዎችን ጨምሮ በርካታ የተለያዩ የጦር መሳሪያዎች ከቡድኑ መማረካቸውን ምንጮቻችን ጠቁመዋል፡፡