ከችግር በላይ ከፍ ብለው የሚሰሩ ብርቱዎችን ማበረታታት፣ ችግራቸውንም መፍታት ተገቢ ነው – ምክትል ከንቲባ አዳነች አቤቤ

ግንቦት 21/2013 (ዋልታ) – የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ አዳነች አቤቤ በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ መርካቶ አማኑኤል ቤ/ክ አካባቢ በ1967 ዓ.ም ተመስርቶ የሚገኘውን የእድገት በስራ ሁለገብ የሸማኔዎች የህብረት ስራ ማህበር ጎብኝተዋል።
የማህበሩ አባላት የሚሰሩበት ሁኔታ አመቺ ባይሆንም፣ ስራቸውን በከፍተኛ ሞራል እና ትጋት እየሰሩ በአክሲዮን ተደራጅተው በዘመናዊ አሰራር
የከተማ አስተዳደሩ እንዲደግፋቸው መጠየቃቸውን ምክትል ከንቲባዋ ገልጸዋል፡፡
ሰራተኞቹ በአብዛኛው አረጋዊያን መሆናቸውን የገለጹት ምክትል ከንቲባ አዳነች አቤቤ “ያሉበት የስራ ሁኔታ ኋላ ቀር እና ምቹ ያልሆነ ሆኖ ሳለ በዚያው ሁኔታ ውስጥ የሚታይባቸው ተስፋ እና ትጋታቸው ስራ ሳያማርጡ እና ሳይንቁ እየሰሩ ለሚቸገሩ ወገኖቻችን አስተማሪ ነው “ብለዋል።
ምክትል ከንቲባዋ “ለእነዚህ ብርቱ እና ትጉ ሰራተኞች ጥያቄ አፋጣኝ ምላሽ እንደምንሰጥ እና እንደምናበረታታ ላሳውቅ እወዳለሁ” ሲሉ በማህበራዊ የትስስር ገጻቸው አስፍረዋል።