ከአሰብ ወደብ ጋር የሚያገናኘው የአስፋልት መንገድ ግንባታ ተጀመረ

ከ2 ቢሊየን ብር በላይ ወጭ የሚሆንበት 71.6 ኪ.ሜ የሚረዝመው ከአሰብ ወደብ ጋር የሚያገናኘው የሜሎዶኒ ማንዳ ቡሬ የአስፋልት መንገድ ግንባታ ዛሬ በይፋ ተጀመረ፡፡

በትራንስፖርት ሚኒስትር ዳግማዊት ሞገስና የአፋር ክልል ርዕሰ መስተዳደር አወል አርባ የመሰረት ድንጋይ አስቀምጠዋል።

ግንባታው ሻንዶንግ ሊኪኖ ግሩፕ በተባለ የሥራ ተቋራጭ እንደሚገነባ ታውቋል።

መንገዱ ከ20 ዓመት በፊት ተገንብቶ አገልግሎት ሲሰጥ የነበረ ሲሆን፣ አሁን ላይ ደረጃውን ከፍ በማድረግ በሲሚንቶና በአስፋልት ኮንክሬት የሚገነባ መሆኑ ተገልጿል።

(በምንይሉ ደስይበለው)