ከኢፌዴሪ የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን አገልግሎት የተሰጠ መግለጫ

ከኢፌዴሪ የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን አገልግሎት የተሰጠ መግለጫ

ኃላፊነት የጎደላቸው አካላት ለአደገኛ የፖለቲካ አጀንዳ ሲባል እየፈጠሯቸው የሚገኙ መሠረተ ቢስ ውንጀላዎችን ኢትዮጵያ ታወግዛለችበምዕራባውያን የተለያዩ አካላት አማካኝነት በኢትዮጵያ ላይ የሚነዙ የሐሰት ስም ማጥፋቶችን የኢትዮጵያ መንግሥት ፈጽሞ አይታገሥም።

እነዚህ አካላት ኢትዮጵያ ውስጥ የከፉ ወንጀሎች ሊፈጸሙ ይችላሉ በሚል የሕወሐትን ጊዜ ያለፈበት ፕሮፓጋንዳ እንደ በቀቀንመድገማቸው አሳፋሪ ነው።

እነዚህ አካላት የሚከሱት ፍንጮችን ወይም ተጨባጭ ክስተቶችን መሠረት አድርገውአይደለም፤ የመፈጸም ዕድል አለ በሚል ያልተጨበጠ ግምት እንጂ።

እጅግ የሚያሳዝነው ደግሞ የተሻለ ስም ያላቸው ተቋማት ሳይቀሩ ይሄንን በኢትዮጵያ ላይ ተቀነባብሮ የሚለቀቅ ፕሮፓጋንዳ ለመቃወም አለመቻላቸው ነው።

ጥቂቶቹም ስለ ኢትዮጵያ የተነገረውን ስምማጥፋት በማመን ሳይሞኙ እንዳልቀሩ ይገመታል። አንዳንዶችም እነዚህን የሐሰት ክሶች ኢትዮጽያን ለማንበርከክ ሊጠቀሙባቸው ይፈልጋሉ።

ይሄን መሰል አስደንጋጭ ክሶችን አቅርቦ የኢትዮጵያ መንግሥትን በማስጨነቅ በሕወሐት ላይ እየወሰደ ያለውን የመከላከል ርምጃ ለማስቀየስ የሚችሉ መስሏቸው ከሆነ ተሳስተዋል።

አንዳንዶችም የሚችሉትን ሁሉ በማድረግ ይህንን ቡድን ለማዳን እየተረባረቡ ነው። አንዳንድ ምዕራባውያን ባለ ሥልጣናት ጭምር ይሄንን የሐሰት ክስ የሚነዙት ኢትዮጵያ ትእዛዛቸውን አልቀበል ስላለቻቸው መሆኑን በይፋ መናገር ጀምረዋል። ይህ ጊዜ አመጣሽ የሐሰት ክስ መሬት ላይ ያለውን እውነታ ጨርሶ አይቀይረውም።

እነዚህ ጉምቱ ተቋማትና ወሳኝ ተዋንያን፣ በቂ ግንዛቤ ሳይኖራቸው በዚህ የሃሰት ዘመቻ እየተሳተፉ ይገኛሉ። ይሄን የመሰሉ የከፉና ሊወገዙ የሚገባቸው ውንጀላዎች ለፖለቲካ ዓላማ መዋላቸው ኃላፊነት የጎደለውና አሳፋሪ ነው።