ከፍተኛ 4ጂ የሞባይል ኢንተርኔት አገልግሎት በጅግጅጋ ይፋ ተደረገ

መጋቢት 30/ 2013 (ዋልታ) –  ኢትዮ ቴሌኮም ከፍተኛ 4ጂ (4G LTE Advanced) የሞባይል ኢንተርኔት አገልግሎት በምስራቅ ምስራቅ ሪጅን ከተሞች በጅግጅጋ ከተማ ይፋ ተደረገ፡፡
ጅግጅጋ፣ ጎዴ፣ ፊቅ፣ ደገሃቡር፣ ቀብሪበያህ፣ ዋርዴር፣ ቀብሪደሀር ከተሞች ነው አገልግሎቱ ይፋ የተደረገው።
የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ሥራ አስፈፃሚ ፍሬህይወት ታምሩ የሀገሪቱን ኢኮኖሚ ወደ ዲጅታል ኢኮኖሚ ለማሳደግ እየተሰራ እንደሚገኝ ገልፀዋል።
በአፍሪካ በቀዳሚነት ቴሌኮም አገልግሎት ያስጀመረው ኢትዮ ቴሌኮም ዘመኑን የሚመጥን ፈጣን የደምበኞች እርካታን የሚያሟላ የኢንተርኔት አገልግሎት በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍል ማስጀመር እንደሚቀጥል ተገልጿል።
በሰባቱ ከተሞች 450ሺህ በላይ ዜጎች ተደራሽ ማድረግ ቢቻልም በሚጠቀሙት የሞባይል ቴክኖሎጂ ውስንነት 180ሺህ ዜጎች አገልግሎቱን የሚያገኙ ይሆናል ተብሏል።
(በሃኒ አበበ)