በውሃ፣ በውሃ ዲፕሎማሲና ኮሙዩኒኬሽን ላይ ትኩረት ተሰጥቶ ሊሰራ እንደሚገባ ተገለጸ

ታኅሣሥ 7/2015 (ዋልታ) በውሃ እንዲሁም የውሃ ዲፕሎማሲና ኮሙዩኒኬሽን ላይ ትኩረት ተሰጥቶ ሊሰራ እንደሚገባው የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር አስታወቀ።

ኢትዮጵያ የአፍሪካ ውሃ ማማ ብትሆንም ያላትን ሀብት በሚገባው ልክ ያልተጠቀመች ሀገር መሆኗን ያነሱት የውሃና ኢነርጂ ሚኒስትሩ ሀብታሙ ኢተፋ (ዶ/ር) የውሃ ሀብቷን የተፋሰስ ሀገራትን በማይጎዳ መልኩ እየተጠቀመች መሆኑን ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ማሳወቅ ይገባታል ብለዋል።

በተለይ ዲፕሎማቶች በምርምር ተቋማት የሚሰሩ ጥናትና ምርምሮችን በሌሎች ቋንቋዎች በመተርጎም የኢትዮጵያን እውነት ማሳወቅ ይኖርባቸዋል ብለዋል።

7ተኛው የውሃ፡ የውሃ ዲፕሎማሲና ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ፎረም ኮሙኒኬሽን ጉባኤ በአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ እየተካሔደ ነው።

በጉባኤው ከፍተኛ የመንግስት ስራ ኃላፊዎችን ጨምሮ በውሃ ላይ ጥናትና ምርምር ያደረጉ ምሁራን  ተገኝተዋል።

ዙፋን አምባቸው (ከአዳማ)