ከ2 ቢሊየን ብር በላይ ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የኮንትሮባንድ እቃዎች መያዛቸው ተገለፀ

መጋቢት 27/2013 (ዋልታ) – ባለፉት ስምንት ወራት ከ2 ቢሊየን ብር በላይ ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የኮንትሮባንድ እቃዎች መያዙን የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ኮንትሮባንድ መቆጣጠርና ኦፕሬሽን ዳይሬክቶሬት አስታወቀ።
በኮሚሽኑ ወንጀል መከላከል ዘርፍ የኮንትሮባንድ ቁጥጥርና ኦፕሬሽን ዳይሬክተር ረ/ኮሚሽነር አይንሻ ቶላ እንደገለፁት፣ የፌዴራል ፖሊስ አባላት ህገ-ወጥ እንቅስቃሴውን ለመቆጣጠር ባደረጉት ጥረት የሚያዘው የእቃ ብዛትና መጠን ከአመት አመት እየጨመረ መጥቷል፡፡
ካለፈው አመት ጋር ሲነፃፀርም የ47 በመቶ ጭማሪ ማሳየቱን ተናግረዋል።
የኮንትሮባንድ እቃዎቹ ወደ ሀገር ቢገቡ በሀገርና በዜጎች ላይ የሚያደርሱት ጉዳት ከፍተኛ በመሆኑ የመከላከልና የመቆጣጠር ስራውን ህብረተሰቡ ሊያግዝና ህገ ወጥ እንቅስቃሴ ሲመለከት ጥቆማ ሊሰጥ እንደሚገባ ኮሚሽነሩ ማሳሰባቸውን ከፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡