ከ200 በላይ የገጠር ከተሞችን የኤሌክትሪክ ተጠቃሚ ለማድረግ እየተሰራ መሆኑ ተገለጸ

ሚያዝያ 10/2015 (ዋልታ) ከዋናው ግሪድ ርቀው የሚገኙ ከ200 በላይ የገጠር ከተሞችን የኤሌክትሪክ ተጠቃሚ ለማድረግ እየሰራ መሆኑን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት አስታወቀ፡፡

አገልግሎቱ በዘርፍ ከተሰማሩ የግል ድርጅቶችና ማህበራት ጋር በመሆን በአዴል ፕሮግራም ከዋናው ግሪድ ርቀው የሚገኙ ከ200 በላይ የገጠር ከተሞችን የኤሌክትሪክ ተጠቃሚ ለማድረግ ስራ መጀመሩን ገልጿል፡፡

በተጨማሪም በብሄራዊ ኤሌክትሪፊኬሽን ፕሮግራም ከዋናው ግሪድ 65 በመቶ እንዲሁም በአማራጭ የኃይል ምንጭ 35 በመቶ የሚሆነውን የህብረተሰብ ክፍል የኤሌክትሪክ ተጠቃሚ ለማድረግ እየተሰራ ነው ተብሏል፡፡

ለፕሮጀክቱ 400 ሚሊየን የአሜሪካን ዶላር አጠቃላይ በጀት የተያዘ መሆኑም ተጠቁሟል፡፡

ፕሮጀክቱ ከዋናው ግሪድ ርቀው በሚገኙ የሀገሪቱ አካባቢዎች የሚኖሩ የህብረተሰብ ክፍሎችን ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚ ለማድረግ እና የኑሮ ሁኔታቸውን ለማሻሻል ያለመ መሆኑን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት መረጃ አመላክቷል፡፡