የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ተቀማጭ ገንዘቡ ከ1 ትሪሊየን ብር በላይ መሻገሩን አስታወቀ

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ

የካቲት 1/2015 (ዋልታ) የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ተቀማጭ ገንዘብ ከ1 ትሪሊየን ብር በላይ መሻገሩን አስታውቋል፡፡

የባንኩ ፕሬዝዳንት አቤ ሳኖ በትዊተር ገፃቸው ባተላለፉት መልዕክት የባንኩ ተቀማጭ ገንዘብ ከ1 ትሪሊየን ብር በላይ ተሻግሯል፡፡

ለዚህም ለሁሉም ባለድርሻ አካላት፣ ለባንኩ ደንበኞች እና ሰራተኞች በሙሉ የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡