ኮሚሽኑ የአርቲስት ሃጫሉን ግድያን ተከትሎ የተፈፀሙ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችን ሪፖርት ይፋ አደረገ

የኢትዮጵያ ሠብዓዊ መብት ኮሚሽን የአርቲስት ሀጫሉ ሁንዴሳን ግድያን ተከትሎ በኦሮሚያ ክልል 40 ከተሞች የተፈፀመውን የሠብዓዊ መብት ጥሰት አስመልክቶ ያዘጋጀውን ሪፖርት ይፋ አድርጓል።

ኮሚሽነሩ ዶክተር ዳንኤል በቀለን ጨምሮ ሌሎች ባለሙያዎች ሪፖርቱን አስመልክቶ ለጋዜጠኞች መግለጫ እየሰጡ ነው።

በከተሞቹ በተደረገው ዳሰሳ 30 ሙያተኞች መሳተፋቸው ተገልጿል።

የቀረበው ሪፖርት ከአርቲስቱ ግድያ ቀን ጀምሮ እስከ ሶስት ቀን የነበረውን ሁኔታ የዳሰሰ ነው።

በዳሰሳው ጉዳት ከደረሰባቸው የመንግስት አካላት ለ328 ሰዎች ቃለ መጠይቅ ተደርጓል፤ የፎቶግራፍ፣ የድምፅና ሌሎችም መረጃዎችና ማስረጃዎችም ተካተዋል።

በዚህም 123 ሰዎች ተገድለዋል 520 ሰዎች ደግሞ ለአካል ጉዳት ተዳርገዋል።