ጠ/ሚ ዐቢይ በጤና ሚኒስቴር የሰው ሰራሽ አካል እና የአካል ድጋፍ ማደራጃ ድርጅትን ጎበኙ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አሕመድ በጤና ሚኒስቴር የሰው ሰራሽ አካል እና የአካል ድጋፍ ማደራጃ ድርጅትን ጎብኝተዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ የሰው ሰራሽ አካል እና የአካል ድጋፍ ማደራጃ ድርጅትን ጉብኝት ያካሄዱት ረፋድ ላይ ነው፡፡
ድርጅቱ ሰው ሰራሽ አካል እና ለመንቀሳቀስ ድጋፍ የሚሆን እንደ ክራንች ያሉትን እና ሰው ሰራሽ አካላትን በማምረት ይታወቃል።