ኮርፖሬሽኑ ያስገነባቸውን የመኖሪያ እና የንግድ ቤት ህንፃዎች እያስመረቀ ነው

ሰኔ 06/2013(ዋልታ) – የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን በአዋሬ ፣ ቶታል ተዘንአ ሆስፒታ አካባቢ ፣ መካኒሳ ገርጂ እና ቦሌ ያስገነባቸውን ደረጃቸውን የጠበቁ የመኖሪያ እና የንግድ ቤት ህንፃዎች እያስመረቀ ነው።
ኮርፖሬሽኑ ገርጂ በሚገኘው ሳይት ለአቅመ ደካሞች 50 ቤቶችን የገነባ ሲሆን 26ቱ ተጠናቀው ለርክክብ በቅተዋል።
ፕሮጀክቶቹ የቤት እጥረትን ከመፍታት ጐን ለጐን ከ5000 በላይ ዜጐች የስራ ዕድል መፍጠር የቻለ ሲሆን ለአዲስ አበባ ከተማ መልሶ መልማት በተጨማሪ ኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ ጠቀሜታቸው የጐላ ነው ተብሏል።
(በሜሮን መስፍን)