ወጋገን ባንክ ለበጎ አድራጎት ድርጅቶች የ825 ሺሕ ብር ግምት ያላቸው የቁሳቁስ ድጋፍ አደረገ

ወጋገን ባንክ

ግንቦት 11/2014 (ዋልታ) ወጋገን ባንክ ለሁለት በጎ አድራጎት ድርጅቶች እና ለወይራ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት 825 ሺሕ ብር ግምት ያላቸው የቁሳቁስ ድጋፍ አደረገ።

ባንኩ የ25ኛ ዓመት የምስረታ በዓሉን ምክንያት በማድረግ ወላጅ አልባ ህፃናትን በመርዳት ላይ ላለ ለዋይድ ሆራይዘን ፎር ችልድረን ኢንኮርፖሬሽን ድርጅት የ225 ሺሕ ብር ድጋፍ፣ ለሙዳይ በጎ አድራጎት ድርጅት ማኅበር 230 ሺሕ የሚገመት የምግብ ቁሳቁስ ድጋፍ እንዲሁም ለወይራ ቅድመ 1ኛ እና የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት 370 ሺሕ ብር የሚገመት የተማሪዎች መመገቢያ ጠረጴዛና ወንበር ድጋፍ አድርጓል።

በድጋፍ ርክክቡ ላይ የተገኙት የባንኩ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ተዋካይ የኋላሽት ዘወዱ ባንኩ ማኅበራዊ ኃላፊነቱን ለመወጣት የተለያዩ ሥራዎችን እየሰራ መሆኑን ገልጸው የኅብረተሰቡን ማኅበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ችግሮችን ለመፍታት እየሰራ መሆኑን ጠቁመዋል።

አሁን የተደረገው ድጋፍም ይህንኑ አጠናክሮ ለመቀጠል መሆኑን አንስተው ባንኩ ወደፊትም ይህን መሰል ድጋፍ ማድረጉን አጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል።

ባንኩ ባአሁኑ ወቅት በመላው የሀገሪቱ ክፍሎች 400 ቅርንጫፎች ያሉት ሲሆን 41 ቢሊየን ብር በላይ ተቀማጭ ሀብት እንዳለውም ተመላክቷል።

በእመቤት ንጉሴ

ለፈጣን መረጃዎች፦
ፌስቡክ https://bit.ly/3Ma7QTW